Menu

  አማርኛ       English                

የጽ/ ቤቱ ሥልጣንና ተግባር

ጽ/ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

  • በአዲስ አበባ ከተማ ያለዉ የትራንስፖርት እና ትራፊክ ማኔጅመንት ማሻሻያ ጥናቶችን በመመርመር ለሚመለከተዉ አካል ያቀርባል፣ ሲፈቀድለትም ይፈጽማል፣ ያስፈጽማል፡፡
  • ከተለያዩ የልማት አጋሮች ጋር በመሆን የተጀመሩ የትራንስፖርት አገልግሎትና የትራፊክ ማኔጅመንት ማሻሻያ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸዉ አቅጣጫ፤ በተገቢዉ ዉልና ስምምነት እንዲሁም የስራ ዝርዝር መሠረት እየተፈጸሙ መሆናቸዉን ይከታተላል፣ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
  • በከተማ ዉስጥ የሚካሄዱ የትራንስፖርት ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ የአገልግሎት ሥራን የሚመራ አካል በመለየት ወይም እንዲደራጅ በማድረግ የአገልግሎት ሥራዉ እንዲጀመር ያደርጋል፤
  • የከተማዉን ትራንስፖርት ለማሻሻል የተመረጡ ፕሮጀክቶች ትግበራ ላይ የአማካሪዎች፣ የአቅራቢዎች እና የኮንትራክተሮች ማወዳደሪያና መምረጫ መስፈርቶች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
  • አጠቃላይ የከተማ ትራንስፖርትና ትራፊክ አመራርን የማሻሻል ሥራዎችን በሚመለከት ቢሮዉን የማማከር ሥራ ያከናዉናል፣
  • እንደአስፈላጊነቱ በቦርዱና በቢሮዉ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናዉናል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አማርኛ