Menu

  አማርኛ       English                

ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ

                  መረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ለአንድ ሀገር ዕድገት ቁልፍ ሚና አለው !!

       1. መግቢያ

የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እና ፈጣንና አስተማማኝ የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት በመፍታት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት የታመነ ነው፡፡ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (TPOM)፣ በተቋሙ ሥር ላሉ ቢሮዎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ድጋፍና ፍላጎታቸውን ለመሟላት የመረጃ ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ደጋፊ የስራ ሂደት ቋቁሟል፡፡ የመመቴክ ደጋፍ የሥራ ሂደት የተለያዩ የመመቴክ ፕሮጀክቶች እቅድ፣ ዲዛይን፣ ትግበራ፣ ማሰፋፋት፣ እና የመማከር ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ በዚህ ረገድ የሥራ ሂደቱ በተቋሙ ስር ላሉት የሥራ ክፍሎች ሙያዊ ድጋፍ፣ የምክር እና የውሳኔ ሃሳቦችን በማመንጨት ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለሚነሱ ፍላጎቶች እና ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የኢኮቴ መሳሪያዎች ግዥ በሚደረግበት ጊዜ ቴክኒካዊ ስፔስፊከሽን የማዘጋጀት እና ተገዝተው ሲቀርቡም በስፔስፊከሽኑ መሠረት መቅረባቸውን የማረጋገጥ ሥራ ይሠራል፡፡ ለሶፍትወሮች እና ሲስተም ልማት ሥራዎችም ዝርዝር የፊላጎት ስፔስፊከሽን  ማዘጋጀት እና ሲስተሞቹ በሚለሙበት ጊዜም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በስፔስፊከሽኑ መሠረት መሠራቱን የማረጋገጥ ሥራ ይሠራል፡፡

የኢኮቴ ዕቃዎች ጥገናና ደህንነት፣ የኢንተርኔት፣ የፕርንተር እና የመረጃ ልውውጥ አገልግሎቶችን ማረጋገጥ፤ የዳታቤዝ እና የኔትወርክ መሠረተልማት ማስፋፋት ሥራዎችም የሥራ ክፍሉ ዋና ዋና ተግባራት ናቸው፡፡

     2የኢ.ኮ.ቴ ደጋፊ የሥራ ሂደት የ2009 በጀት ዓመት ግቦች

ግብ  1፡- የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማና ግብረ-መልስ ስርዓት ማሳደግ፣  

 ግብ  2፡- የቢሮ ግብዓት ማሟላት፣

ግብ  3፡-በማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ወቅታዊ፣አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ማዕከል መገንባትና የኔትወርክ መሠረተልማት ማስፋፋት፣

ግብ  4፡-በማስተበሰበሪያ ጽ/ቤቱ ሥር ለተደራጁ የሥራ ክፍሎች ፈጣንና አስተማማኝ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ድጋፍ መስጠት፣

ግብ  5፡-በጽ/ቤቱ ለሚቀረጹ ፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞች የኢ.ኮ.ቴ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት፣ 

      3. የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች 

3.1. ዳታ ቤዝና ሲስተም ማስተዳደር

§  አጠቃላይ የሲስተሙን ስራ በመከታተል ለታቀደለት አላማ እንዲውል ማስቻል፤

§  ለሲስተሙ ስራ መፋጠን የሚያገለግሉ ግብአቶች እንዲሟሉ ማድረግ፤

§  ሲስተም ጥናት በማድረግ ተገቢውን ማሻሻያ ወይም ቴክኖሎጂ እንዲተገበር ማድረግ፣

§  የመረጃ ቋቱን አሰራርና ፍጥነት በማጥናት ሀርድዌር እና ሶፍትዌር ማሻሻያዎች ማድረግ፤

§  የዳታ ቤዙ አሰራር በተፈለገው መልኩ መሆኑን መከታተል፤ ችግሮች ሲያጋጥሙ ማስተካከል፤

§  በወቅቱ የሲስተሙን መረጃ ባክአፕ መውሰድና መረጃው ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ፤

§  ለተጠቃሚዎች የይለፍ ኮድ መስጠትና መቆጣጠር፤

§  የሲስተሙን ፀረ-ቫይረስ ወቅታዊ መሆኑን መከታተል፤

§  ሁሉም አፕሊኬሽን ሶፍትዌሮች እና የሰርቨሮችን ብቃት (performance) እና ደህንነት መከታተል፤

      3.2. የኔትወርክ አስተዳደርና ጥገና

§  የኔትወርክ ተጠቃሚዎች መቆጣጠርና በአግባቡ ማስተዳደር፤

§  አጠቃላይ የኔትወርክ አሰራር ብቃት (performance) በመከታተል እንዲስተካከል ማድረግ፤

§  ለኔትወርክ ስራ መፋጠን የሚያገለግሉ ግብአቶች እንዲሟሉ ማድረግ፤

§  በተቋሙ ደረጃ ጥቅም ላይ የሚውሉ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ መሣሪያዎች እና ሌሎች የተቋሙ መገልገያ የሆኑ ኮምፒውተርና ተጓዳኝ እቃዎች ስፔስፊኬሽን ማዘጋጀት፤

§  ለሚገዙ ኤሌክተሮኒክስ እቃዎች እስፔሲፊኬሽን ማዘጋጀት፤

§  የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ መሳሪያዎቹና አጠቃላይ የተቋሙ የኮምፒውተር መሣሪያዎች በስፔስፊኬሽኑ መሠረት መገዛታቸውን ማረጋገጥ፤

§  ሰርቨር ኮምፒውተሮችን የቢሮ ማሽኖችን ቴሌኮም እቃዎችን መጠገን/ እንዲጠገኑ ማድረግ፤

§  የመረጃ መረቡ ግንባታና ተከላ የሚያገለግል ጨረታ ዶክመንት ማዘጋጀት፤

§  ፀረ-ቫየረስ በመጫንና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም የሲስተሙን ደህንነት መጠበቅ፤

§  ተጠቃሚዎች በየጊዜው ተጨማሪ እውቀት እንዲኖራቸው ድጋፍና ስልጠና መስጠት፤

§  ስራ ሂደቶች የመረጃ አያያዛቸው ዘመናዊ እንዲሆን ድጋፍ ማድረግ፤

 

 

አማርኛ